Sunday, 8 May 2016

መዝሙር ምንድነው?

መዝሙር፦ማለት ዘመረ፣አመሰገነ ከምለው ከግዕዝ ቃል የመጣ ሰሆነም.. . ምስጋና ፣ልመና (መማጸን)፣መደሰት ወይም ማስደሰት ፣ማዜም ማለት ነው።
{ዜማ } ነው።
ስለ መዝሙር የበለጠ ማብራሪያ ከመጽሐፍ ቅዱስ መዝ 94፡1-3 ፤ 149፡1፤150፡1፤ 80፡1-3፤ ማቴ 26:40፤ ማር 14፡2፤ 11:9 ኢስ 35፡1፤ ሉቃ 19:38
ማንበብ ይቻላል  ።
       መዝሙር አምልኮ ነው።
ልዑል እግዚአብሔር የሚመሰገንበት የሚወደስበት የሚቀደስበት መንገድ ነው።
እንግዲህ ይህን ሀሳብ ስናነሳ መዝሙር መቼ ተጀመረ የሚለው ሀሳብ ብነሳ መልካም ይመስለኛል።
መዝሙር የተጀመረው በእግዝኣሔር ዙፋን በሰማይ  ነው።
ማን ነው የጀመረው ክዱሳን ማላዕክት። ኢስ 35፡1፤6፡1፤ራዕ 4፡4
ቀን የላቸውም ለሊት 24 ሰኣት ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ይዘምሩታል ለአምላካችን ።
ቀጥሎ ደግሞ እስራኤል የኤራን ባህር ተሻግረው በበህር ማዶ የሙሴ እህት ማርያምና የእስረኤል ህዝብ ዘምረዋል።ዘጸ15፡1
ሰለዚህ ዝማሬ አምልኮ ነው።
መዝሙር በተለያየ ስሜት መገለጫነት ይዘመራል
      ፨በድል ጊዜ
      ፨በሀዘን ጊዜ
      ፨በለቅሶ ጊዜ
መዝሙር ስብከት ነው።

No comments:

Post a Comment